አንተ የምትሰራቸውን ማንም ሊሰራ አይችልም

መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዚህ ምድር ላይ እየተመላለሰ ባስተማረው ትምሕርትና ባደረጋቸው ታላላቅ ገቢረ ተአምራት ያመኑና አምላክነቱን የተቀበሉ ብዙ ሰዎች ነበሩ። በአንጻሩ ትምሕርቱንና ገቢረ ተአምራቱን ተመልክተው ከራሳቸው ጥቅም አንጻር በማየት የጥቅማቸው ተቀናቃኝ የመጣ መስሏቸው የሚቃወሙትም ነበሩ።

ሙሉውን ያንብቡ>>

ታማኝ አገልጋይ ማን ነው?

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በምሳሌ ሲያስተምር መንግስተ ሰማያት አገልጋዮቹን ጠርቶ ለአንዱ አምስት፣ ለአንዱ ሁለት፣ ለአንዱ አንድ መክሊትን ሰጥቶ ወደ ሩቅ አገር የሄደን ባለጸጋ ሰውን ትመስላለች። ባለጸጋው መክሊቱን የሰጣቸው ለእያንዳንዳቸው እንደየአቅማቸው ነው። ሥራ እንዲሰሩበትና እንዲያተርፉበት ነው። መክሊቱንም ከሰጣቸው በኋላ ወደ እሩቅ አገር ሄደ።

ሙሉውን ያንብቡ>>

ሰው የለኝም

ብዙውን ጊዜ ሰዎች በተለያየ ምክንያት ተስፋ ሲቆርጡ ከሚያሰሙት ድምጽ ውስጥ አንዱ ሰው የለኝም እኔ እንደሆንኩ ብቸኛ ነኝ የሚለው ነው። ወገን ዘመድ ኃይል ገንዘብ የለኝም የሚሉ ቃላትን ሲያዘወትሩ ይደመጣሉ። እነዚህንና እነዚህን የመሳሰሉ ቃላት ዝም ብለው የሚመጡ ሳይሆን ሰዎች ታመው የሚድኑ፣ አጥተው የሚያገኙ፣ ተርበው የማይበሉ፣ ወድቀው የማይነሱ...

ሙሉውን ያንብቡ>>

ቤቴን የንግድ ቤት አታድርጉት

ለስሙ ክብር ምስጋና ይሁንና ጌታችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደዚህ አለም መጥቶ በምድር ላይ በሚመላለስበት ጊዜ በቤተ መቅደስና በምኩራብ እየተገኘ ወንጌልን ሰብኳል። የተለያዩ ገቢረ ተአምራቶችን በነዚህ ሥፍራዎች ተገኝቶ ፈጽሟል። በአሥራ ሁለት ዓመቱ በዓል ለማክበር ከእመቤታችንና ከቅዱስ ዮሴፍ ጋር ኢየሩሳሌም ወዳለው ቤተ መቅደስ ሄዶ ነበር።

ሙሉውን ያንብቡ>>

እነሆ ተወልዷል!

«ህፃን ተወልዶልናልና፥ ወንድ ልጅም ተሰጥቶናልና፥ አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል፤ ስሙም ድንቅ መካር፥ ኃያል አምላክ፥ የዘላለም አባት፥ የሰላም አለቃ ተብሎ ይጠራል»ኢሳ 9፥6 የተባለው ትንቢት ይፈጸም ዘንድ ሰማይና ምድር የማይችሉት አምላክ በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ማርያም በአጭር ቁመት በጠባብ ደረት ተወሰነና በቤተልሔም ተወለደ።

ሙሉውን ያንብቡ>>

ጌታችን በእውነት ተነስቷል

ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሰውን ልጅ ከዘላለማዊ ሞት ለማዳን በመስቀል ላይ ተሰቅሎ ከሞተ በኋላ ከመስቀል አውርደው ማንም ሰው ባልተቀበረበት በአዲስ መቃብር የአርማቲያሱ ዮሴፍና ኒቆዲሞስ ገንዘው በክብር ቀብረውታል።

ሙሉውን ያንብቡ>>

ሰላም ለእናንተ ይሁን

‹‹የሰላም አለቃ››ኢሳ 9፡6 ተብሎ የተነገረለት መድኃኔዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ ለደቀ መዛሙርቱ ያሰማው የሰላም መልእክት ነው። ሰላም በዕለተ ዓርብ በመስቀሉ ላይ ተሰብኳል። በሲዖል ለነበሩት ነፍሳት የሰላም ነፃነት ታውጇል። ደቀ መዛሙርቱ ግን ጌታ በአይሁድ እጅ ተላልፎ ከተሰጠበት ጊዜ ጀምሮ የሚያዩትና የሚሰሙት ሰላም አሳጥቶ አስጨንቋቸዋል።

ሙሉውን ያንብቡ>>

ሆሳእና በአርያም!

ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሰውን ልጅ ከዘላለማዊ ሞት የማዳን ሥራ ለመፈጸም ጥቂት ቀናት ሲቀሩት በነቢያት የተነገረው ትንቢትና በብሉይ ኪዳን የነበረው ምሳሌ ይፈጸም ዘንድ በአህያይቱና በውርንጫው ላይ ተቀምጦ ወደ ኢየሩሳሌም ሲገባ ደቀ መዛሙርቱና ብዛት ያለው ሕዝብ ‹‹ሆሳዕና በአርያም›› እያሉ በመዘመር ሰማያዊ አዳኝ መሆኑን መስክረው ተቀብለውታል።

ሙሉውን ያንብቡ>>

መስቀል ኃይላችን ነው

ከመስከረም 16 ቀን እስከ 25 ድረስ ያሉት ቀናት መስቀል የሚል ስያሜ ተሰጥቷቸዋል። ብርሃነ ዓለም ቅዱስ ጳውሎስ ለቆሮንቶስ ሰዎች በጻፈው መልእክቱ «የመስቀሉ ቃል ለሚጠፉት ሞኝነት ነው ለእኛ ለምናምን ግን የእግዚአብሔር ኃይል ነው»1ኛ ቆሮ 1፥18 ብሏል።

ሙሉውን ያንብቡ>>
Donate