አንተ የምትሰራቸውን ማንም ሊሰራ አይችልም

መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዚህ ምድር ላይ እየተመላለሰ ባስተማረው ትምሕርትና ባደረጋቸው ታላላቅ ገቢረ ተአምራት ያመኑና አምላክነቱን የተቀበሉ ብዙ ሰዎች ነበሩ። በአንጻሩ ትምሕርቱንና ገቢረ ተአምራቱን ተመልክተው ከራሳቸው ጥቅም አንጻር በማየት የጥቅማቸው ተቀናቃኝ የመጣ መስሏቸው የሚቃወሙትም ነበሩ።

ታማኝ አገልጋይ ማን ነው?

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በምሳሌ ሲያስተምር መንግስተ ሰማያት አገልጋዮቹን ጠርቶ ለአንዱ አምስት፣ ለአንዱ ሁለት፣ ለአንዱ አንድ መክሊትን ሰጥቶ ወደ ሩቅ አገር የሄደን ባለጸጋ ሰውን ትመስላለች። ባለጸጋው መክሊቱን የሰጣቸው ለእያንዳንዳቸው እንደየአቅማቸው ነው። ሥራ እንዲሰሩበትና እንዲያተርፉበት ነው። መክሊቱንም ከሰጣቸው በኋላ ወደ እሩቅ አገር ሄደ።

ሰው የለኝም

ብዙውን ጊዜ ሰዎች በተለያየ ምክንያት ተስፋ ሲቆርጡ ከሚያሰሙት ድምጽ ውስጥ አንዱ ሰው የለኝም እኔ እንደሆንኩ ብቸኛ ነኝ የሚለው ነው። ወገን ዘመድ ኃይል ገንዘብ የለኝም የሚሉ ቃላትን ሲያዘወትሩ ይደመጣሉ። እነዚህንና እነዚህን የመሳሰሉ ቃላት ዝም ብለው የሚመጡ ሳይሆን ሰዎች ታመው የሚድኑ፣ አጥተው የሚያገኙ፣ ተርበው የማይበሉ፣ ወድቀው የማይነሱ...

Donate