ቤተ ክርስቲያናችን ኮቪድ19 ተብሎ የሚጠራው ዓለም አቀፍ ወረርሽን በምእመናን ላይ እያስከተለ ያለውን መንፈሳዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ስነ ልቦናዊ ተጽዕኖ ለማቃለል የሚሰራ የአስቸካይ ጊዜ ግብር ኃይል አቋቁማ እየተንቀሳቀሰች ነው።

ይህ ዓለም አቀፍ ወረርሽኝ ሁላችንንም በአንድም በሌላም መልኩ የጎዳን ቢሆንም በርካታ ምእመናንን ግን ለከፍተኛ የኢኮኖሚያዊ እና ስነልቦናዊ ቀውስ ዳርጓል። በዚህ አስቸጋሪ ጊዜ ላይ ቤተ ክርስቲያንችሁ ከጎናችሁ ሆና አስፈላጊውን እገዛ ሁሉ በአቅሟ ለማድረግ ዝግጁ ከመሆኗም በላይ ምእመናንን መደገፍ እና መጠበቅ ከአምላኳ የተሰጣት ኃላፊነትም ስለሆነ በከፍተኛ ደስታ የምትፈጽመው ተልዕኮዋ ነው። ስለዚህ የተለያየ እርዳታ የምትሹ ወገኖች ከታች እንድትመዘገቡ ታበረታታለች።

ቤተ ክርስቲያንችን ለዚህ ጉዳይ ትኩረት ሰጥታ በጀት የመደበችለት ቢሆንም የእርዳታውን ተደራሽነት ለማስፋት ግን ግብረ ኃይሉን በተለያየ መንገድ ማገዝ የምትፈልጉ ምእመናን እንድትሳተፉ ታበረታታለች። ስለሆነም ከዚህ በታች ባለው ቅጽ እርዳታ ለማድረግ እንድትመዘገቡ እንጠይቃለን።

Donate