አትላንታ መካነ ሕይወት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ የኢ. ኦ. ተ. ቤ. ክ. Atlanta Mekane Hiwot Abune Gebre Menfes Kidus EOTC
"የጻድቅ መታሰቢያ ለበረከት ነው" ምሳ 10:7
Monday, January 7, 2013
Tuesday, October 2, 2012
መስቀል ኃይላችን ነው
ከመስከረም 16 ቀን እስከ 25 ድረስ ያሉት ቀናት
መስቀል የሚል ስያሜ ተሰጥቷቸዋል። ብርሃነ ዓለም ቅዱስ ጳውሎስ ለቆሮንቶስ ሰዎች በጻፈው መልእክቱ «የመስቀሉ ቃል ለሚጠፉት
ሞኝነት ነው ለእኛ ለምናምን ግን የእግዚአብሔር ኃይል ነው»1ኛ ቆሮ 1፥18 ብሏል። ይህ መልእክት በተላለፈበት ዘመን ይኖሩ
የነበሩት የአብርሃም ዘሮች ነን የሚሉ አይሁድና ለሥጋዊ ጥበብ ከፍተኛ ቦታ ይሰጡ የነበሩ ግሪኮች የክርስትናን እምነት በራሳቸው
አመለካከት ለመረዳት የሚሹ ነበሩ። የክርስቶስን የማዳን ጥበብ ለመረዳት አይሁድ በአይናቸው ተአምራትን ለማየት ሲሹ የጥበብ
ሰዎች ነን የሚሉት በሥጋዊ ጥበብ የመስቀሉን ቃል ሊመራመሩ ፈልገዋል። ይህ ምስጢር ግን የሚገለጠው በእምነት ለሚፈልጉት ስለሆነ
የመስቀሉ የማዳን ሥራ ከእነርሱ ሊሰወር ችሏል።
Subscribe to:
Posts (Atom)